ጥቅምት 12/2018

የማኅበራችን አዲሱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስትቲዩት አቶ ጌታቸው ነጋሽ የኢንስትቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና የጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንዲሁም ወ/ሮ አስቴር ተክሌ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጋር የትውውቅ ፕሮግራም ተደርጓል። ላለፉት ዓመታት የነበረውን ጠንካራ ግንኙነት በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል በጋራ ልንስራባቸው ሚገባቸውን ጉዳዮች ለይተን ተወያይተናል። ኢንስትቲዩቱም በቱሪዝም ዘርፍ ዋነኛ ተዋናይ ከሆነው የቱሪስት አስጎብኚ ባለሞያ ጋራ የቴክኒክ ቡድን በማቋቋም በእቅድ ላይ የተመሰረተ ዝርዝር የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት ተግባራትን እንድናሳልጥ አፅንኦት ሰጥተዋል። በአጠቃላይ በትብብር አብሮ በመሠራት ለሀገራችን የቱሪዝም ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለማድረግ የሰመረ ውይይት አድርገናል።