Today, October 16, 2025 starting 01:30PM, our association (Ethiopian Tourist Guides Professionals Association) had the privilege of paying a meaningful visit to the Adwa Victory Memorial Museum. The visit was more than a tour; it was an engaging and productive dialogue with the museum’s leadership, centering on shared interests in preserving and promoting Ethiopia’s greatest heritage, Adwa.
As one of the key stakeholders in the sector, our association raised and discussed a number of points that reflect both the broader tourism landscape and our professional engagement:
1. Tourism-related discussions
• How to make the museum’s security checkpoints more visitor-centered, ensuring a friendly and more engaging experience for guests
• Strategies to enrich the museum’s collection with additional artifacts that reflect its historical and geographic significance
• Considerations on the museum entrance fees
2. Association-focused discussions
• Establishing a relationship for closer collaboration between the museum and our association
• Creating an exclusive visit and training that might allow our professional member guides to be able to guide through the museum
• Exploring ways to use the museum’s facilities for future events and programs organized by our association
Finally, we extend our heartfelt appreciation to the museum’s management for their warm welcome, their openness to dialogue & their commitment to working collaboratively.
የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማኅበር የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎበኘ!!
ጥቅምት 6 ቀን 2018ዓ.ም
ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 07፡30 ጀምሮ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በነበረን ቆይታ ፍሬያማ የሆነ የጉብኝት እና የውይይት ጊዜ የነበረን ሲሆን ፤ በመድረኩም እንደ ዋና የሙዝየሙ ባለድረሸ አካል በርከት ያሉ የቱሪዝሙን እና በተለየ ደግሞ የማኅበራችንን ጥያቄ አቅርበን ተወያይተናል፡፡
ከተነሱ አጀንዳዎች መካከል
1. አጠቃላይ ከቱሪዝሙ ጋር በተገናኘ
• የሙዚየሙ የፍተሻ መንገድ ጎብኚን ያማከለ የሚሆንበትን መንገድ
• ሙዚየም ከያዘው ቦታ እና ታሪክ አንፃር ተጨማሪ ቅርሶችን ማሰባሰብ በሚቻልበት መንገድ
• የሙዚየሙን ክፍያ በተመለከተ
2. ቀጥታ ከማኅበራችን ጋር በተገናኘ
• ከማኅበራችን ጋር በጋራ መስራት በሚያስችሉን አጠቃላይ ጉዳዮች በተመለከተ
• ሌላ ሰፊ የጉብኝት እና የስልጠና መድረክ ስለሚፈጠርበት ሁኔታ እና ከሙዚየሙ አስጎብኚ ባለሙያዎች በተጨማሪ የእኛ ማኅበር አባላት የሆኑ አስጎብኚ ባለሙያዎች ሙዚየሙን የማስጎብኘት ፍቃድን በተመለከተ
• ማኅበራችን ለሚያከናውናቸው የተለያዩ ኩነቶች ሙዚየሙ ያለውን መገልገያ ቁሶች እና ቦታዎችን ለመጠቀም የሚያስችሉ መንገዶችን በተመለከተ
የሚሉት ጥቂቶቹ ነበሩ።
ማኅበራችን ለሙዚየሙ ኃላፊዎች ስለተደረገልን መልካም መስተንግዶ እና የውይይት መድረክ የከበረ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማኅበር!!