የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ!!!

The Ethiopian Tourist Guides Professionals Association (ETGPA) successfully held its Annual General Meeting (AGM) on September 6, 2025 at the Ethiopian Heritage Research Authority Hall.

Prior to the meeting, members received a comprehensive documents; including the annual activity and financial reports, the proposed work plan for the 2018 Ethiopian Calendar (EC) fiscal year & two new agenda items for approval.

The AGM was marked by thoughtful & productive discussions and meaningful engagement from members; where several important decisions were made, all, aiming at strengthening the future of our association.

Key decisions approved by the General Assembly included:

1. Approval of the 2017 (Ethiopian Calendar) Fiscal Year Reports

(Covering the period from July 8, 2024 to July 7, 2025); both the activity and financial reports were reviewed and officially approved.

2. Amendment of the Association’s Article

A proposal to revise a specific article in the Association’s Memorandum was presented and approved.

3. Establishment of ETGPA “Idir”

The proposal to create an indigenous & internal support initiative (ETGPA እድር / Idir) was approved in principle. However, the General Assembly recommended that the draft document be circulated among all members to gather additional input and constructive suggestions before final implementation.

4. Election of New Executive Committees

The General Assembly approved the election of Seven ETGPA Executive Committee Members to serve for the next two years (One Service Term). The elected members are:

4.1 Ashenafi Sileshi – President

4.2 Yonas Tiku – Vice President

4.3 Fasil Abebe – Secretary General

4.4 Henok Tsegaye – Public Relation

4.5 Bisrat Mesfin – Treasurer

4.6 Wutsifte Girma – Cashier

4.7 Yigermal Getu – Executive Committee Member

የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

ጳጉሜ 1 ቀን 2017ዓ.ም

ማኅበራችን (የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማኅበር) በጳጉሜ 1 ቀን 2017ዓ.ም በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናት ባለስልጣን አዳራሽ ውስጥ በነበረው ጠቅላላ ጉባኤ በአጀንዳነት በተዘረዘሩት መሠረታዊ አጀንዳዎች ላይ ገንቢ እና ውጤታማ የሆነ ውይይቱን ካከናወነ በኋላ ማኅበሩን ለወደፊት ይጠቅማሉ ብሎ ያሰባቸውን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡ በዋናነትም

1.  የአመቱን የክንውን ሪፖርት ፣ የሒሳብ አፈፃፀም እና የመጪው ጊዜ (2018ዓ.ም) ዕቅድ ሪፖረትን በጥልቀት ከተመለከተ በኃላ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

2.  ከማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ በዚህ ሰዓት ቢሻሻሉ ይጠቅማል ብሎ ያመነባቸውን ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተወያይቶ በአብላጫ ድምፅ አሻሽሏል፡፡

3.  የማኅበሩን መረዳጃ እድር ለመመስረት የሚያስችል አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

4.  በመጨረሻም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫውን በመግባባት እና የማኅበሩን ጥቅም ሊያስከብር በሚያስችል መልኩ አግባብነቱን ጠብቆ አከናውኗል፡፡

በዚህም መሠረት የመጪው ሁለት ዓመት የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማኅበር ሰባት (7) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጦ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡

ተመራጭ ስራ አስፈፃሚ አባላቱም፡-

  1. አቶ አሸናፊ ስለሺ (ፕሬዘዳንት)
  2. አቶ ዮናስ ትኩ (ምክትል ፕሬዘዳንት)
  3. አቶ ፋሲል አበበ (ፀኃፊ)
  4. አቶ ሔኖክ ጸጋዬ (ህዝብ ግንኙነት)
  5. አቶ ብስራት መስፍን (ሂሳብ ሹም)
  6. ወ/ውፅፍተ ግርማ (ገንዘብ ያዥ) እና
  7. አቶ ይገርማል ጌቱ (የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል) ሆነዋል፡፡